መግቢያ

ልማታዊና  ዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችን ፈጣንና ምላተ ህዝቡ የሚሳተፍበትን እድገት በማምጣትና የህዝቡን ዙሪያ መለስ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ክልላችንና አገራችንን በማያቋርጥ የእድገት አቅጣጫ ማራመድ የሚያስችል ስርዓት ነው፡፡

ለስርዓቱ መምጣጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ፀረ-አብዮት በነገሰበት ፖለቲካና ኮረቲ በሩቅ የሚል አመለላከት በሰፈነበት እንዲሁም ደርግን ታሎ መጣል ተራራ በገመድ መጎተት ነው የሚል የተስፋ ቆራጮችና ጨለምተኞች አስተሳሰብ የበላይነት በያዘበት ወቅት የአላማ ፅናት በነበራቸው የህዝብ ልጆች የተመሰረተው ኢህዴን/ብአዴን ነው፡፡

በሀገራችን የብሔር፣ ብሔረሶችን ህዝቦች እኩልነት የተረጋገጠበት ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት እንዲመሰረት የታገሰው ኢህዴን/ብአዴን ከ1973-1983 ዓ.ም መላ የአማራን ህዝቦች በደጀንነት በማሰለፍና ከሌሎች ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባካሄደው መራራ የትጥቅ ትግል ተጋድሎ የፋሽስቱን ስርዓት መጣል ችሏል፡፡

በዚሁ የትጥቅ ትግል ወቅት በርካቶች ህይዎታቸውንና አካላቸውን አጥተዋል፡፡ ለዚህ ታላቅ አላማ ስኬታማ መሆን ሲታገሉ ለተሰውና አካላቸውን ላጡ ሰማዕታት እንሱን ሊዘከር የሚችል በማስፈለጉ የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታተ መታሰቢያ ሐውልትን በመገንባት የታለመለትን ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

የሀውልቱ ዋነኛ መልዕክት የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም ብሄረ አማራ በፍፁ ሊታጠፍ የማይችል ፅኑና ዘላቂ አላማ እንዳላቸው ማረጋገጥ ነው፡፡ ሌላቸው አላማ ለተሰጠው ሰማዕታ አክብሮት የመስጠት ተልዕኮንም ሀውልቱ ተጎናፅፏል፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ሀውልቱ የቆመላቸውና ለመታሰቢያነት የተበረከተላቸው ሰዎች ትግሉን ከዚህ ደረጃ አድርሰው እነሱ አልፈዋል፡፡

ሰላምን፣ ልማትንና ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ የሚካሄድ ትግል ደግሞ አንድ ሰው ጀምሮ የሚጨርሰው ሳይሆን በቅብብሎሽ የሚጓዝ ነው፡፡ ሀውልቱ ያለፉት ሰማዕታት ጀምረው ከዚህ ደረጃ ያደረሱትነ የተከበረ አላማ ተቀብለን ወደ ፊት ልናራምደው እንደሚገባ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ ኢህዲን/ብአዴን የአማራ ህዝቦች የትግል ፍሬ ነው፡፡

ኢህአፓን ተቃውመው የወጡ ታጋዮች ከጎንደር ወደ ትግራይ ምድር ተሻግረው ቆላ ተንቤን ውስጥ በሚገኝ አንድ ጫካ የመሠረቱት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊን ቅናቄ ኢህዴን/ብአዴን/  እልህ አስጨራሽ፣ረጅምና ውስብስብ የትግል ጉዞ የተጋፈጡትን ፈርጀ ብዙ ፈተና፣ክቡር ዓላማቸውን በማሳካት ረገድ የተቀዳጆቸው ድሎችን የምንዘክርበትን ሀውልት በተመለከተ መዘክር በሚል ርዕስ ብአዴን የሁኑ አዴፓ 1998 . የሰማዕታት ህያው መታሰቢያ በሚል ርዕስ ያሳተመውን ጽሁፍ መነሻ በማድረግ ሀውልቱ በቅርጽና ይዘቱምን ይመስላል የሚለውን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ሆነው ያገኘኋቸውን አንኳርአንኳር ነጥቦች ለግንዛቤ እየቀነጫጨብኩ ለማቅረብ እሞክራለሁ። መልካምንባብ!

1985 . የአማራ መታሰቢያ ሀውልትን ለመገንባት ዲዛይን ለማሰራት ለሳዓሊያን ጥሪ ቀረበ፡፡…ለሳዓሊያኑም የፈጠራ ስራቸውን ያለ አንዳች ፖለቲካዊ ተጽዕኖ በሙሉ የፈጠራ መብትና ነጻነት እንዲጠበቡና እንዲያከናውኑ ተገለጸላቸው፡፡…በወቅቱ አራት ሰዓሊያን ዲዛይናቸውን ለሚመለከተው አካል አቀረቡ፡፡…

የሀውልቱን ግንባታ በተመለከተ በምሰዓሊያን የጥበብ ፈተናውን ለመጋፈጥ፣የጥበብ ጉጉታቸውን ለማሳካት፣የጥበብ ነፃነታቸውንና ኃላፊነታቸው ለመውጣት፣የጥበብ ውጤታቸውንም ለማየት፣ራዕያቸውን አስቀመጡ፣የፈጠራ ሂደታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ለፈጠራው ሂደት መነሻና ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉትን መረጃዎችንና ዋቢዎችን አሰባሰቡ፡፡

በግብዓትነትም፡-

ከብአዴን/አዴፓ የተገኙ የቃልና የፅሁፍ መግለጫዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ሰሙ፣አነበቡ፣

ልዩልዩ የፎቶግራፍ ሰነዶችን ተመለከቱ፣አዩ፣

የብአዴንና/አዴፓ የህዝብን የትግል ሂደትና ትስስር ተረዱ፣ የብአዴን/አዴፓ ታጋዮችንና የህዝቡን ትጥቅና አለባበሶች ተመለከቱ ወዘተ…

ሰዓሊያን በተገኘው መረጃ ላይ በመመርኮዝና በማጥናት አማካኝ የተፈጠ ሀሳብ እስኪደርስ ድረስ በተከታታይ ተወያዩ ደጋግመው ተከራከሩ፣ሀሳብ ለሀሳብ ተለዋወጡ፣በመጨረሻም የፈጠራውን ፅንሰ ሀሳብ አንኳር መነሻ አገኙ፡፡

ሰዓሊያን በሚከተሉት ነጥቦች ላይ እንዲመሰረቱ ወሰኑ ይኸውም በይዘቱ በተፈጥሮና በሰው ልጅ አንፃራዊ ክስተት ላይ ተመስርቶ ሀለት ዓይነት መንገድ እንዲቀርብ፣

ማለትም፡-

ኪነ-ሀውልት /Monument/

በቀዳሚነትና በዋነኝነት ለሰማዕታቱ መታሰቢያ በረዥሙ የሚቆም

ኪነ-ቅርፆች /Sculptures/

ለሰማዕታቱ መታሰቢያ በቀዳሚነትና በዋነኝነት የቆመውን ኪነ-ሀውልት በማጀብ የህዝቡንና የብአዴንን/አዴፓን ትግል ሂደት ታሪክ የሚተርክ እንዲሆን ተግባቡ ፡፡ ወሰኑ  ፡፡      

በቅርፁ – በተለይ ኪነ-ሀውልቱ በአይነቱ

ወጥና ልዩ፣ /Original/

ቁጥብ፣እምቅ፣ግልፅናቀላል፣

ጥበባዊ ውበቱን የጠበቀ፣

ለተመልካች አዲስ የማይዘነጋና የማይረሳ፣

ለአገነባብ የሚመች፣

ከቦታው ጋር የሚስማማ፣

ወዘተ…ሆኖ እንዲቀርብ ሲወስኑ፣

በውሳኔው ላይ ደጋግመው፣ በትናንሽ ኪነ-ንድፈቶችም (Sketches) ሙከራ አደረጉ፣ በይዘቱም ሆነ በቅርፁ መዘንጋት የሌለበትን ጥበባዊ ነገር- ስንና/esthetics/ ስነ-ምግባር (Ethics) እንዲያሟላ አስፈላጊውን ጥረት አደረጉ፡፡

ይኸውም፡-

በአለማቀፋዊነቱና በሁለንተናዊነቱ፣ማለትም በሰው ልጅ ሰብዓዊነቱ፣እኩልነት፣ሰላምና ነፃነት የተመሰረተእንዲሆን፣ሌላው ቁም ነገር በብሄራዊነቱና በወገናዊነቱ ላይ ሲሆን በጭቁኑ የአማራ ህዝብ ማንነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፣

በተለይ፡-

በብአዴን/አዴፓ የትግል ፅናት ላይ፣

በህዝቡና በብአዴን/አዴፓ አንድነት ላይ፣

በመራራና በፈታኝ የትግል ዘመናት ላይ፣

በማሸነፍና በመሸነፍ ጊዜያት ላይ፣             

በመስዕዋትነትና በድል ጊዜያት ላይ፣

በተከሰቱ እውነታዎች ሁነቶች /realities and events/ ዙሪያ፣ ሂደቶችና ማስተጋብራቱ የፈጠ\ቸውን ታሪኮች፣ በማገናዘብና በማስተዋል ከጽንሰ ሀሳብ ወደተጨባጭ ትልቅ ስዕላዊ ኪነ- ንድፍ መንደፍና / /መተርጎም ፣ከሀሳብ ወደ እይታ መለወጥ ተሸጋገሩ፡፡

ሰዓሊያን ስለ ኪነ-ሀውልቱና ስለ ኪነ-ቅርጹ ይዘትና ቅርፅ፣ ጥበባዊ የፈጠራ ሂደት ስሜትና እሳቤ፣ ድርሰትና ቅንብር፣ የሚደርሱበትን፣ የደረሱበትንና የሚያሳድሩት  አተረጓጎም እንዲህ ይላሉ፡፡

በጥበባዊ ይዘቱ፡-

ሀ. በተፈጥሮና በሰው ልጅ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ኑባሬ፣ስርዓት፣

ለ. የሁለትና /duality/ አንፃራዊ ተቃርኖንና ኑባሬን /duality of opposites and harmony/

ሐ. በተፈጥሮና በህብረተሰብ ውስጥ ያለውን የሰው ልጅ ህልውና እና የመኖር ጥያቄ /essence and existence/

መ. በሚያልፈው እውነትና በማያልፈው ሀቅ /reality and truth/ መካከል ያሉትን ልዩነቶችና አንድነቶች፣ በንፅፅር በማጥናት፣ በማገናዘብ በማስተዋል፣ ሰብዓዊና አለማቀፋዊ የጥበብ ፍልስፍናዎችንና አስተሳሰቦችን በማመሳጠርና በማዋሀድ፣ ጥበባዊ ይዘቱ ዘላለማዊነት እንዲያገኝ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል – ይላሉ ሰዓሊያኑ::

ሀ/ በድግግማዊ ሚዛንም ምጥጥን /rhythmical balance and proportion/

ለ/ በንፍቃዊና-ኢንፍቃዊ ምጥጥን /symmetrical and asymmetrical balance and proportion/

ሐ/ በጥበባዊ የድርሰትና የፈጠራ አቀነባበር እንዲሁም ቀመራዊ ስሌት፣ታይቷል፣ታድሷል፡፡

ሰዓሊያኑ ሲያብራሩት ፡-

ሀ. ኪነ-ሀውልቱ ተምሳሌታዊ ረቂቅ /symbolical, abstract/ ነው፡፡

ለ. ኪነ-ቅርፆቹ እውነታዊና ወካይ ናቸው፡፡ /realistic, representational/

ኪነ-ሀውልቱ ከሩቅ ይታያል፣ በመታየቱም ይጠራል፣ በቀላሉ ይታወቃል፣ ይለያል፣ ይታወሳል፣ ያስታውሳል፡፡

ከቅርብሲታይበተምሳሌትነቱናበረቂቅነቱየሚኖረውናየሚይዘውትርጉምእጅግጥበባዊናቅኔያዊጥልቅናምጡቅቁምነገርነው፡፡ደጋግመውና ልብ ብለው ሊመለከቱት የሚገባ የውስጥና የውጭ ክፍሎች አሉት፡፡

ኪነ-ሀውልቱ ከውጭ ሲታይ ወንዴና ሴቴ ነው፡፡ ደረት ለደርት በመገጠሙና በሚተያዩ በመንታና ንፍቃዊ ዓምዳዊነት በ40 ሜትር ከፍታ መቆምን ልብ ይሏል፡፡ ህብረ ቀለማዊ መልኩም ከውስጥ ደረት ለደረት የሚታየው ክፍል ነጭ ነው፡፡በውጭ በኩል ህብረ ቀለማዊ መልኩ ጥቁርና ነጭ ነው፡፡

ሶስት ንዑስ ክፍሎች አሉት፡፡የታች፣የመሃልና የላይ ናቸው፡፡በታች በስድስት ተሸካሚ አዕማድ ላይ ቆሟል፡፡

ህብር ቀለማዊ መልኩ ጥቁር ነው፡፡ተምሳሌትና ትርጉማቸው፡፡

አንድና ብዙ /one and many/

የህዝብን አንድነትና ድጋፍ ይወክላል፡፡

ጥቁሩ የመከራና የትግል ዘመንን ያስታውሳል፡፡

ከመሀል፡-ክብ ሞሰብ መሰል /ወይም ዲስክ/ በስድስቱ ተሸካሚ እዕምድ ላይ ይገኛል፡፡ከክቡ ስር አብለጭላጭ የመደብ ቀለበት ይገኛል፡፡ህብር ቀለማዊ መልኩም ነጭ ነው፡፡

ተምሳሌትና ትርጎማቸው፡-

ብአዴንና ማዕከላዊ አመራሩን፣

ድርጅቱንና አንድነቱን ይወክላል፣

ነጩ የትግልና የድል ዘመንን ጥራት ይታወሳል፡፡

ከላይ፡- መሀል ለመሀል በንፍቃዊ ዓምዳት ለሁለት የተካፈለና ደረት ለደረት በእኩልነት የቆመ ይገኛል፡፡

ህብር ቀዳማዊ መልኩ ነጭና ጥቁር ነው፡፡

ተምሳሌትና ትርጉማቸው፡-

ሴትና ወንድን ይወክላሉ፡፡

2- ኪነ-ሀውልቱ ከውስጥ ሲታይ፡- መታሰቢኒቱን ለመዘከር በስድስት ተሸካሚ አዕማድ መሀል ባሉት በር መሰል ወደ ውስጥ የሚገባ እንግዳ በቅድሚያ በወለሉ መሀል ላይ እሳት ሲበራ ያያል፡፡

ተምሳሌትና ትርጉሙ፡-

ዘላለማዊነትን፣መስዕዋትነትን፣እራሱ ተቀጥሎ ለሌሎች ብርሃን መሆንን ይወክላል፡፡የውሃ ጠብታ ቀስበቀስ ሲንጠባጠብ ይስተዋላል፡፡

ተምሳሌትና ትርጉሙ ለትግሉ የፈሰሰውን ደምና ላብ ይወክላል፡፡

ከውሃ ገንዳ ጎን አፈር መኖሩን ያስተውላል፡፡

ተምሳሌቱንና ትርጉሙ ደግሞ ለማንነት ክብር በአገሩ የወደቀውን ታጋይና ለትግሉ አፈር የለበሱትን ይወክላል፡፡

አየር /ነፋስ/ በቢሮዎቹ በአንዱ ወይም በሌሎች በኩል ሲነፍስ ይሰማል፡፡

ተምሳሌቱንና ትርጉሙ ለትግሉ ትንፋሹን ውጦና ተንፍሶ ዳገትና ቁልቁለት ወርዶ ወጥቶ የታገለውን ታጋይ እስትንፋይወክላል፡፡በጥቅሉ አራቱ ባህሪያትን /

እሳት፣ ውሃ፣ መሬትና አየርን / የእናት ምድርን ምንነትና የራስ ማንነትን ይወቅላሉ፡፡

በዚሁ ድባብ ውስጥና ስድስቱ አዕማድ የተሸከሙት መጠነ በ5 ሜትር ከፍታ የሆነ እንቁላል መሰል (Dome) ጣሪያ፣ በመሃሉም የብርሃን ማስገቢያ መስታውት ይገኛል፡፡ ህብረቀለም መልኩም ነጭ ነው፡፡ በዚህም ነጭና ብርሃናማ ድባብ ውስጥ ገብቶ የቆመና ሰማዕታቱን መዘከር የፈለገ እንግዳ የህሊና ጸጥታ እረፍትና ሰላም እየተላበሰ የብአዴንን ትግልና መስዕዋትነት ጥንካሬና ፅናት ያስታውሳል፡፡ ይገነዘባል፡፡

ይኸውም በአንፃራዊነት፡- አንድነት ከሁለትነትና ከብዙነት ይነሳል፣ ህያውነት በመኖር ውስጥ ይከሰታል፣ ድል ከመስዕዋትነት ያብባል፣ ዘላለማዊነት ከህልፈት ይገኛል፡፡ እነዚህ በተፈጥሮም ሆነ በህብረተሰብ ውስጥ ያሉ የማይነጣጠሉና የሚኖሩ ናቸው፡፡ ይላሉ- ሰዓሊያን፡፡

ኪነ-ሀውልቱና ገፅታው

ኪነ-ሀውልቱ አራት ገፅታ አሉት፡፡ የፊትና የጀርባ፣ የቀኝና የግራ፡፡ የፊቱ ገፁ ወደ አባይ ወንዝ በኩል ያለው ሲሆን ጀርባው ደግሞ በአንፃሩ ያለው ነው፡፡ የፊትና የጀርባ ገፅታውን የሚመለከት አንድ ሰው ገፅታው አንድ ዓይነት ሊመስለው ይችላል፡፡ ወይም ልዩነት ያለው አይመስለውም፡፡ ልብ ብሎ ለተመለከተው ግን ልዩነቱ ግልፅ ነው፡፡

ከአባይ ወንዝ በኩል ሆኖ ወደ ላይ የኪነ-ሀውልቱን የፊት ገፅታ ሲመለከት የኪነ-ሀውልቱ ግራና ቀኝ ውጫዊ የጎን ጠርዞች፣ አንዱ የአንዱን ወይም የቀኙ የግራውን አይደግምም፡፡ አይመስልም፡፡ ሴቴው በስተግራ፣ ወንዱ በስተቀኝ መሆናቸውን በቀላሉ ይረዳል፣ በጀርባ ገፁ ሲታይ እንዲሁ ወንዱ በስተግራ፣ ሴቴው በስተቀኝ መሆናቸውን ይገነዘባል፡፡

እንዲሁም በኪነ-ሀውልቱ በስተግራና በስተቀኝ ጎኖች በኩል ያሉት ገፆች ተዘዋውሮ ለሚያይ ልዩነቱን በጉልህ ይረዳልል::                           

ነጭና ጥቁር ሰላምና ጦርነትን፣ መስዕዋትነትንና ድልን ይወክላል፡፡

የኪነ-ሀውልቱ የጥቁርና ነጭ ህብር ቀለማት መልክ መፈራረቅ ደግሞ የልዩነቱን ድግግማዊ ምጥጥን ከነገረ- ስነ-ጣዕም /aesthetical taste/ ጋር ሳይሰለቸን ወይም ሳይጨንቀን፣ ሳይንዛዛብን ወይም ሳያጥረን እንድናስተውል ይጋብዙናል፡፡ ይህም የሚሆነው ከኪነ-ጥበባዊ ቅርፅ አኳያ ሲስተዋል ነው፡፡

በጥበባዊ ይዘቱ ግን የሚያመለክተው አንድነትንና ውህደት ነው፡፡ አንፃራዊነታቸው የአንድነታቸው ረቂቅ ተምሳሌትና ትርጉም አለውና፡፡ አንዴት ቢባል አንዱ ያለአንዱ አይኖርም፡፡ ማለትም፡- ጥቁርና ነጭ፣ ጨለማና ብርሃን፣ ወንድና ሴት ወዘተ ሁለትም አንድም ናቸው፡፡

ነገር ምክንያቶችን ሁሉ በዚህ ኪነ-ሀውልት ይወክላል፣ ይታወሳል፣ ይዘክራል፣ እንዳይረሱም ያደርጋል፡፡

ኪነ-ቅርፆች፡-

በቀዳሚነትና በዋናነት ኪነ-ሀውልቱን በማጀብና በማድመቅ፣ የትግሉን ታሪካዊ ጀማሪና ፍፃሜ በወካያዊና በእውነታዊ ኪነ-ቅርፆች /representational and realistic sculpture/ መግለፅ ነው፡፡

ኪነ-ቅርፆቹ ዘላለማዊ ጥንካሬያቸውን እንዲያገኙ በመደብ ቅርፅ የተሰሩ ወይም የተቀረፁ ናቸው፡፡ በሁለት ንዑስ ክፍሎች ተከፍለዋል፡፡ ከኪነ-ሀውልቱ በስተፊትና በስተጀርባ በኩል በተራኪነት ቁመዋል፡፡

ከኪነ-ሀውልቱ ፊትለፊት ወረድ ብሎ በርቀት የሚገኘው ኪነ-ቅርፅ ወደ አባይ ወንዝ ፊቱን አድርጎ ይገኛል፡ ይህ ኪነ-ቅርፅ በራሱ በሶስት አውታር መጠንና በሁለት አውታር መጠን የኪነ-ቅርፅ አይነቶች /three diamensional sculpture and two diamensional relief/ ለሁለት ተከፍሎ የተቀረፀ ነው፡፡

ኪነ-ቅርፃዊ አቀማመጡ ኪነ-ቅርፁ /sculpture/ ከላይ ሲሆን፣ ኪነ-ፍልፍል ቅርፁ /relief/ ከስር ይገኛል፡፡

ከላይ፡- ኪነ-ቅርፅ ቅንብሩ አቀነጃጃቱ፣

ኢ-ንፍቃዊ ቅንብር ነው፡፡ ፊትና ኃላ አለው፡፡

ከፊት፡- ያሉት የተወሰኑ በቁጥር አምስት በአንድ አካባቢ

ለድል የበቁ፣ ያሸነፉ፣

ረጅሙን የትግል ዓመታት በፅናት የፈፀሙ,

በነቃና በተደላደለ አቋም ተስፋቸውን የሚያዩ፣

ያለፈውን የትግል ዓመታት የሚያስታውሱ፣ የታጋዮችና የህዝቡ /የአርሶአደሩ/ ተወካዮች ሲገኙ፣

ከኃላ ያሉት፡- የተወሰኑ በቁጥር ሁለት

በመስዕዋትነት የወደቀ ጋይ፣

የወደቀውን ጀግና ለማንሳት የቀረችበት እናት ያገኛል፡፡

በዚህ የሶስት አውታር መጠን ኪነ-ቅርፁ ቅንብር ውስጥ በቁጥር ሰባት ምሰለ አካል /Figures/

ወጣትና ሽማግሌ /አዛውንት/

ህፃንና ጎልማሳ፣

ወንዶችና ሴቶች ይገኛሉ፡፡

በአጭሩ ታጋዩና ህዝቡ ባንድነት ለአንድ አላማና ለአንድ ግብ ተሰልፈውና ድል አድርገው ይገኛሉ፡፡

ከስር፡-

የኪነ-ፍልፍሉ ቅርፅ ቅንብር፡- በታሪክ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ኪነ-ቅርፁ በቆሙበት መደብ ስር በሁለት ገፁ ጎንና ጎን በኩል እንደ ሰሌዳ ተለጥፈው ይገኛሉ፡፡

የሚተርኩትም የትግሉን ሂደት ነው፡፡

ይኸውም፡-

የህዝቡን ጉስቁልና፣መከራና ስቃይ፣

ለአመፅና ለትግል መነሳሳትን፣

የብአዴንን/አዴፓ አመራርናትግል፣

በነፃ መሬት /የትምህርት፣የእርሻ ወዘተ/

በጦርነትና በድል ጎዳና፣

ወዘተ የተካሄደውን ተግባርና ከጅማሬ እስከ ፍፃሜ ይተርካል፡፡  ኪነ-ቅርፁ በቆመበት መደብ ስር ደግሞ በፊት ለፊት የብአዴን አርማ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ ኪነ-ቅርፁ በውሃ የተከበበ ነው፡፡

ከኪነ-ሀውልቱ በስተጀርባ፡-

በመግቢያው ደረጃ መጀመሪያ ላይ ሁለት ኪነ-ቅርፆች አንፃር ለአንፃር በትይዩ ቆመዋል፡፡ አቋቋማቸውም፡- ሀዘንና ደስታ፣ ትዝታና ተመስጥኦን፣ ጅማሬንና ፍፃሜን ያመላክታል፡፡

እናት ልጇን አቅፋ፣

አባት /አዛውንት/ ጠመንጃቸውን አዘቅዝቀው፣

ያላቸው ተምሳሌትና ትርጉም፡-

ሴትና ወንድን፣       

የህዝቦች እኩልነትና ነፃነት ለማረጋገጥ የታገሉና መስዕዋት የሆኑ ሰማዕታትን ዓላማና ስኬት ዘላለማዊ ስምክርነት ለመስጠት፣የኪነ-ህንጻውን ደህንነት መጠበቅ ፣ ታሪካዊና ስነ-ጥባባዊ መረጃዎችን በዘመናዊ መንገድ ማደራጀት፣ ተቋሙ የተመረጠ  የጥናትና ምርምር ማዕከል ማድረግ፣ የህብረተሰቡ መዝናኛና መዳረሻ ማድረግና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት የተቋሙን ገቢ ማሳደግ፡፡

ህፃንነትንና አዛውንትነትን /ትውልድ/ ይወክላሉ፡፡

ሌላው መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ በኪነ-ሀውልቱ ውስጥ የምትንጠበጠበው የውሃ ጠብታ በትግሉ የፈሰሰውን ደምና ላብ የሚያጠይቅ ሲሆን የውሃ ጠብታዋ ቀስ በቀስ የምንጭ ያህል አድጋ ፊት ለፊት ወደ አባይ ወንዝ አቅጣጫ ወደ ውጭ በመውጣት ወደ ታች የምትፈስ ትሆናለች፡፡ አልፎም ወደ ጅረት ተቀይራ ወደ ታች እየወረደች እንደ ፏፏቴ እየበዛች ወደ ኪነ ቅርፆቹ ጋ ስትደርስ ኪነ-ቅርፆችን በመከበብ በመጨረሻም ቀስ ብላ የጀመረችው ጠብታ በዝታና ሰፍታ የሚንፎለፎል ፏፏቴ በመሆን እንደ ገባር ወንዝ ከአባይ ጋር ትቀላቀላለች፡፡

ይህየውሃጠብታ፣ምንጭ፣ጅረት፣ፏፏቴ ሆኖ መፍሰስና ከአባይ ጋር መቀላቀሉ ተምሳሌትና ትርጉሙ እጅግ ሚስጥራዊና ቅኔያዊ ነው፡፡