ስለ እኛ

 ተልዕኮ

ነፃነት ለማረጋገጥ የታገሉና መስዕዋት የሆኑ ሰማዕታትን ዓላማና ስኬት ዘላለማዊ ስምክርነት ለመስጠት፣የኪነ-ህንጻውን ደህንነት መጠበቅ ፣ ታሪካዊና ስነ-ጥባባዊ መረጃዎችን በዘመናዊ መንገድ ማደራጀት፣ ተቋሙ የተመረጠ  የጥናትና ምርምር ማዕከል ማድረግ፣ የህብረተሰቡ መዝናኛና መዳረሻ ማድረግና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት የተቋሙን ገቢ ማሳደግ፡፡

             ራዕይ

መታሰቢያ ሀውልቱ ለሰላም፣ ለዴሞክራሲና ለልማት ለታገሉና ለተሰው ሰማዕታት ህያው ታሪክ መዘከሪያ፣  የላቀ አገልግሎት መስጫ፣ የተደራጀ  የመረጃ ማዕከልና  ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ሆኖ በ2012 ማየት፡:

የተቋሙ እሴቶች

የትግሉን ሙዚየም ማስጎብኘት፣   የታላላቅ ሰዓሊያን አርት ጋለሪ ጉብኝት፣የኪነ-ሀውልት ጉብኝት፣    የኪነ-ቅርፅ ጉብኝት፣የአምፊ ትያትር መድረክ አገልግሎት፣ የአዳራሽ አገልግሎት፣የፏፏቴና ፋዉንቴን  አገልግሎት፣     የጋርደን ጉብኝት አገልግሎት፣የሰርግና ዲኮር አገልግሎት፣ የኢንተርኔት አገልግሎትየዲጅታልና መደበኛ ቤተ-መፃፍት አገልግሎት፣ የመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት ከተጠናከረ ጥበቃ ጋር ይሰጣል፡፡

ስልክ 

058 218 03 78

   0582180381

ፋክስ

   058 218 17 64

መልክት ሳጥን ቁጥር

  1561

ፊስቡክፔጅ አድራሻ፡-

Amhara people martyrs memorial monument

ዌብ ሳይት አድራሻ፡-WWW.amharasemaetate.gov.et

የተቋሙ የኃላ ታሪክ

የሰማዕታት ጽ/ቤት ምስል

የሰማዕታት ጽ/ቤት ምስል

በአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት ጽ/ቤት

ኢህአፓን ተቃውመው የወጡ ታጋዮች ከጎንደር ወደ ትግራይ ምድር ተሻግረው ቆላ ተንቤን ውስጥ በሚገኝ አንድ ጫካ የመሠረቱት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ኢህዴን/ብአዴን/  እልህ አስጨራሽ፣ ረጅምና ውስብስብ  የትግል ጉዞ የተጋፈጡትን ፈርጀ ብዙ ፈተና ፣ ክቡር ዓላማቸውን በማሳካት ረገድ የተቀዳጆቸው  ድሎችን የምንዘክርበትን ሀውልት  በተመለከተ መዘክር በሚል ርዕስ ብአዴን በ1998 ዓ.ም  የሰማዕታት ህያው መታሰቢያ በሚል ርዕስ ያሳተመውን ጽሁፍ  መነሻ በማድረግ ሀውልቱ በቅርጽና ይዘቱ ምን ይመስላል የሚለውን  ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ሆነው ያገኘኋቸውን አንኳር…አንኳር ነጥቦች  ለግንዛቤ  እየቀነጫጨብኩ  ለማቅረብ  እሞክራለሁ። መልካም ንባብ!…

… በ1985 ዓ.ም የአማራ መታሰቢያ ሀውልትን ለመገንባት ዲዛይን ለማሰራት ለሳዓሊያን ጥሪ ቀረበ ፡፡ …ለሳዓሊያኑም የፈጠራ ስራቸውን ያለ አንዳች ፖለቲካዊ ተጽዕኖ በሙሉ የፈጠራ መብትና ነጻነት እንዲጠበቡና እንዲያከናውኑ ተገለጸላቸው፡፡ … በወቅቱ አራት ሰዓሊያን ዲዛይናቸውን ለሚመለከተው አካል አቀረቡ፡፡ …

የሀውልቱን ግንባታ በተመለከተም ሰዓሊያን የጥበብ ፈተናውን ለመጋፈጥ ፣  የጥበብ ጉጉታቸውን ለማሳካት፣ የጥበብ ነፃነታቸውንና ኃላፊነታቸው ለመውጣት፣ የጥበብ ውጤታቸውንም ለማየት፣ ራዕያቸውን አስቀመጡ፣ የፈጠራ ሂደታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ለፈጠራው ሂደት መነሻና ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉትን መረጃዎችንና ዋቢዎችን አሰባሰቡ፡፡

በግብዓትነትም፡-

ከብአዴን የተገኙ የቃልና የፅሁፍ መግለጫዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ሰሙ፣ አነበቡ፣

ልዩ ልዩ የፎቶግራፍ ሰነዶችን ተመለከቱ፣ አዩ፣

የብአዴንና የህዝብን የትግል ሂደትና ትስስር ተረዱ፣ የብአዴን ታጋዮችንና የህዝቡን ትጥቅና አለባበሶች ተመለከቱ ወዘተ…

ሰዓሊያን በተገኘው መረጃ ላይ በመመርኮዝና በማጥናት አማካኝ የተፈጠራ ሀሳብ እስኪደርስ ድረስ በተከታታይ ተወያዩ ደጋግመው ተከራከሩ፣ ሀሳብ ለሀሳብ ተለዋወጡ፣  በመጨረሻም የፈጠራውን ፅንሰ ሀሳብ አንኳር መነሻ አገኙ፡፡

ሰዓሊያን በሚከተሉት ነጥቦች ላይ እንዲመሰረቱ ወሰኑ ይኸውም በይዘቱ በተፈጥሮና በሰውልጅ አንፃራዊ ክስተት ላይ ተመስርቶ በ2 ዓይነት መንገድ እንዲቀርብ፣

ማለትም፡-

ኪነ-ሀውልት /Monument/

በቀዳሚነትና በዋነኝነት ለሰማዕታቱ መታሰቢያ በረዥሙ የሚቆም

ኪነ-ቅርፆች /Sculptures/

ለሰማዕታቱ መታሰቢያ በቀዳሚነትና በዋነኝነት የቆመውን ኪነ-ሀውልት በማጀብ የህዝቡንና የብአዴንን ትግል ሂደት ታሪክ የሚተርክ እንዲሆን ተግባቡ ፡፡ ወሰኑ  ፡፡

በቅርፁ – በተለይ ኪነ-ሀውልቱ በአይነቱ

ወጥና ልዩ፣ /Orginal/

ቁጥብ፣ እምቅ፣ ግልፅና ቀላል ፣

ጥበባዊ ውበቱን የጠበቀ፣

ለተመልካች አዲስ የማይዘነጋና የማይረሳ፣

ለአገነባብ የሚመች፣

ከቦታው  ጋር የሚስማማ፣

ወዘተ… ሆኖ እንዲቀርብ ሲወስኑ፣

በውሳኔው ላይ ደጋግመው፣ በትናንሽ ኪነ-ንድፈቶችም (Sketches) ሙከራ አደረጉ፣ በይዘቱም ሆነ በቅርፁ መዘንጋት የሌለበትን ጥበባዊ ነገር- ስንና/aesthetics/ ስነ-ምግባር (Ethics) እንዲያሟላ አስፈላጊውን ጥረት አደረጉ፡፡

ይኸውም፡-

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *